Gudumaale

   Sidaamu Daga Budu Battala
Connecting Sidama People

ሀዋሳ፤ ፈር ባጣው “አምልኮ ተቋማት” የታነቀች ከተማ

June 6, 2018

መቼም በዛሬው ዘመን ማለትም በ21ኛው ከፍለ ዘመን የሰዎች እንቅስቃሴ በአብዛኛው በግለሱ የግል ውሳኔ ላይ የተመሰረተ እንደሆነ የታወቀ እውነት ነው፡፡ ሰዎች ቢያነስ በመሪህ ደረጃ ወደ ፈለጉበት ይንቀሳቀሳሉ፣ የፈለጉትን መንፈሳዊና አለማዊ ፍልስፍና(spiritual and secular philosophy) ዘርፍ ይከተላሉ፤ያስተምራሉ እንዲሁም ደግሞ ተከታዮችን ያፈራሉ፡፡ ይህ መሆኑ በአንድ ባንድ በኩል የራሱ አዎንታዊ ገጽታ ሲኖረው በሌላ በኩል ደግሞ አሉታዊ ጎኖች ይኖሩታል፡፡ ዜጎች ሀሳባቸውን በነፃነት(ያለገደብ ማለት አይደለም) ይገልጻሉ፣ ይማራሉ ወይም ያስተምራሉ የሚለው መሰረታዊ የመብት ሀሳብ አዎንታዊ ገጽታ ሲኖረው ቢሆን ኖሮ ይበል የሚያስብል ነገር ነው፡፡ በተለይም በአንዳንድ አምባገነናዊ ስርዓት ህዝብን ለከፍተኛ መከራ ዳርጎ በቆየበት እንደ ኢትዮጵያ አይነት ሀገራት(ኢትዮጵያ፣ አፍርካ) ነገሩ ትንግርትም ጭምር የመሆን እድሉ የሰፋ ነው፡፡ ምክንያቱም እንደኢትዮጵያ ያሉ ሀገራት “አንድ ሀይማኖት፣ አንድ ቋንቋ፣ ባህልና የኑሮ ዘይቤ” የሚሉ አስተሳሰቦችና ተግባራት በስፋት ተራምደው በነበረባት ሀገር ግለሰቦች እዚህም እዝያም የፈለጉትን የሀይማኖት አይነት መርጠው መንቀሳቀስ “ከቀድሞ ስርዓት” ጋር እራሱን ለሚያነጻጽር ግለሰብም ሆነ ቡድን እጅግ ጥሩ ማሳያ ሆኖ የሚያገለግል እንደሆነ ከኢህአዴግ የሚበልጥል ሌላ ማሳያ ነገር የአይኖርም፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ፈር ያጣው ወይንም መሪህን የጣሰ “አምልኮ ተቋማት” ፈር ተከትሎ እዲንቀሳቀስ ካልተደረገና ሀይ ባይ ካጣ ወደ አላስፈላጊ ንግድና ማጭበርብር ሊዛመት ከመቻሉም በላይ ትውልድን ወደተሳሳተ አቅጣጫ የመንዳት እድሉ ሰፊ በመሆኑ አዚህ ጋር አሉታዊ ገጽታውን ይዞ ብቅ ማለቱ የግድ ነው፡፡ “የአምልኮ ተቋማት” መስራችና መሪ የሆኑ አካላትም ሰዎችን በተለይም ወጣቶችን ያልተጨበጠ ተስፋ በመመገብ “ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ” ኑሮ እንዲገፉና በሞራል የወደቀ ዜጋ ለሀገሪቷ የማሳቀፍ እድልም ሰፊ ነው ብሎ ያምናል የዚህ መጣጥፍ አዘጋጅ፡፡

እንዴት?
አንዴት ማለት ጥሩ ነው(ጠያቂ ትውልድ ከተገኘ)፡፡ ከላይ በተገለጸው አኳኋን ማለትም መንግስት የእምንት እኩልነት ያከብራል የሚለው ሀሳብ ተከትሎ ሀይማኖቶች በጎጥም ጭምር እየተደጋገሙ መምጣታቸው ዜጎችን ስለምኖራቸው ሀብት፣ ሊመጣባቸው ያለውን አስደንጋጭ ክስተት ከመዘርዘር አልፈው የተባለውን ሀብት ለማግኘት ወይም ከሚመጣባቸው ክፉ ነገር ለመዳን ለተቋማት(ነብይም ይላሉ) መስራችና መሪ ማምጣት ስለምጠበቅባቸው እጅ መንሻ በመዘርዘር የሳምንቱን ቀናት ሙሉ ሊባል በምችል መልኩ በተቋሙ ስለምያቆዩዋቸው ዜጎች በተለይም ወጣቶች በእጅ አዙር ጠባቂነት ቀንበር ስር እየወደቁ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ፈጣሪ ሰርተህ ብላ ያለውን መርህም በተሳሳተ መንገድ ከማስተማርም አልፈው ለወጣቱ ከንቱ ተስፋ በመመገብ እያሳቱ ይገኛሉ፡፡
እዚህ ላይ አንደ ወዳጄ ያጋጠመውን በግርምት ያጫወተኝን ላካፍላችሁ፡፡ አንዲት ሴት ተከራይታ ከሚትኖርበት ቤት ውስጥ በ“መንፈስ” መሞላቷን ተናግራ በተከራየችው ቤት ውስጥ “ጸሎት፣ ዝማሬ…” በመዘውተሩ ምክንያት ሌሎች ተከራዮችን ከማወክ አልፋ ጎሮቤትን መረበሹን ያጠኔው አከራይ ቤቱን እንዲትቅለት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣት እንደማትለቅ ነግራው አረፈች፡፡ ለምን ብሏት ጌታ ይህንን ቤት እንደምሰጠኝ “መልዕክት መቶልኛል” አለች ይለኛል ጓደኛዬ፡፡ 
ይህንን ነው አንግድህ ከንቱ ተስፋ ያለኩት ውድ አንባቢዎች፡፡ ምክንያቱም መቼም ፈጣሪ አያዳላም የሚል እምነት በሁሉም ፈጣሪ አለ የምል መሰረተ-እምነት የሚከተል ማኂበረሰብ ዘንድ የማይጠፋ እውነት ነው፤ እኔም ዘንድ፡፡ ፈጣሪ አያዳላም ከተባለ ደግሞ ቤት ሰሪው ግለሰብ የሰራውን(በላቡ ያፈራውን ብለን እንውሰድ) ቤት አስለቅቆት ለጸላየዋ ሴት በመጣላት “መልዕክት” መሠረት “መንፈሱ” ያስረክባል በለን ካመንን እምነታችን የተሳሳተ ከመሆኑም በላይ የቤቱ ባለቤት በቱን ለቆ መውጣት ፈጣሪን አድሏዊ ያደርጓል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ግለሰቡ የተሻለ ቤት አግንቶ “መልዕክት” ለመጣላት ሴት የተከራየችበትን ቤት በነፃ ይተውላታል(በመንፈስ አስገዳጅነት መሆኑ ነው) ከተባለም መልዕክት የመጣላት ሴት የፀለየችው ለሰማይ መንግስትና ጽድቁ ካለመሆኑም በላይ ያልሰራችውን(ያልሰራ አይብላ የሚል መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሪህ የጣሰ) በመንፈስ አላካ ተቀራመተች ይሆናል፡፡በዚህ አግባብ ሴትየዋ የከንቱ ተስፋ እስረኛ ትሆናለች ማለት ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ለታሰረችለት እጀንዳ በታማኝነት ሳምንቱን ሙሉ ጊዜዋን ትሰጣለች፡፡ ይህም ሰርቶ መብላት የሚለውን መሪህ ስለምጥስ ሀጥአት ይሆናል ማለት ነው፡፡ 
ወደ ዋና ሀሳብ ሲመለስ አንዳንድ ሰርቆ ሀብት ያፈሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች በርሃብ ጠነ እየተገረፈ ላለው፣ በድርቅና ቸነፈር ተመተው ላሚገኙ ለሀገራቸው ዜጎች ያልዘረጉትን እጅ በ“እምነት ተቋማት” መሪዎች የሚደርሳቸውን ስነ-ልቦና ጫና በስርቆት ምክንያት የሚሰማቸውን ከፍተኛ ጭንቀትና በ“እምነት ተቋማት” መሪዎች የሚደርስባቸውን ማስፈራሪያና ተከትሎ ሚመጣውን ከጥፋት መዳኛ ከንቱ ተስፋ በመመገብ የተቀራመቱትን ሀብትና ንብረታቸውን አሳልፈው ላላውቁት ነገር ግን “ነብያችን” ላሉት በመስጠት ከጭንቀት የተገላገሉ መስሎ እንዲሰማቸው ለማድረግ ከመጣርም አልፈው በስርቆት የተገኘውን ሀብት ለማንጻት ጥረት ያደርጋሉ፡፡
በሌላ በኩል አንዳንዶቹ ሀብትና ክብር ሳይለፉበት ከሌላው የበለጠ ለማግኘት “ነብያት”ን ለግላቸወ በገንዘባቸው ገስተዋል፡፡ የተገዙ “ነብያት”ም የተገዙለትን ምድራዊ አጀንዳ ለማሳካት ይተጋሉ፡፡ ታዲያ እነዚህ “ነብያት” ለገዢያቸው ጥሩ ጥሩን መተንበይ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለሀብታሙ (ሀብት ከየትና እንዴት እንደመጣ መንፈሳቸው አይነግራቸውም) ሀብት ይጨመርልሃል/ሻል፣ ለባለስልጣን ደግሞ(ስልጣን የወሰደበትን አካሄድ የሚተች መንፈስ አልተሰጣቸውም) ስልጣን ይጨመርልሃል/ሻል በማለት ህዝብን አየገዛ አነሱን ማጥገቡን እንዲቀጥል ይተነብያሉ፡፡ ባለስልጣኑን በስልጣኑ እንደምገዛ እንጂ ህዝብን ስለበደለ ኢግዚአብሔር እንደተቆጣው አይናገሩም፡፡አድር ባይ ነብይ ይሉታል ይሄ ነው!
ሌባና ጉበኛውን ኢግዚአብሔር የሚጠየፈውን ጉቦ ተቀብለህ ሀብትና ንብረት አካብተሃልና ኢግዚአብሔር ናቀህ ከማለት ይልቅ በሚቀጥለው አመት ሀብትህ በእጥፍ ያድጋል ማለት ይቀናቸዋል፡፡ ጉርሻ ይፈልጋሏ!
ባለስልጣናት በስልጣናቸው መባለጋቸውን፣መኩራራታቸውንና፣ ህዝቡ በመበደሉ የተነሳ ወደ ፈጣሪ እንደጮሄ ለገዛቸው ባለስልጣን ደፍሮ አይናገሩም፤ ህዝቡ በደልን እዳይታገስም በመጽሐፍ ቅዱስ የተደገፈ ነጻነት አያስተምሩም ወይም ባለስልጣናትን ከተግባራችሁ ተቆጠቡ፣ ህዝብን ነጻ አድርጉ ከማለት ይልቅ ስልጣን የሰጠው ፈጣሪ መሆኑን፣ ታጣቂ የታጠቀው በከንቱ አንዳይደለ ከመጽሐፍ ቅዱስ እየጠቀሱ ዜጋውን እያሸማቀቁ ለዘገዢዎች ቀጥና ለት ብሎ እንዲገዛ ይሰራሉ፡፡
በሌላ በኩል ሀይማኖተኛ የሆነ ፖለቲካ መንካት ሀጥአት እስክመስል ድረስ የድፍረት የተሞላበትን ድርጊት እስከመፈጸም ከማድረሳቸውም በላይ ህዝቡን(በተለይም ወጣቱን) ነገሮችን ማገናዘብ እስክያቅተው አድርሰዋል፡፡ የመንግስት አካላትም ስርዓቱን የሚፈታተን/የሚሸነቁጥ ዜጋ አይፈጠርበት አንጂ ዝም ብሎ የቢያመልኩ፣ ዝም ብሎ አርሴ፣ ማንቼ ….ቃና…ቅብርጥሴ ብሉ(አይዝናኑ አላልኩም)፣ “አምልኮ ተቋማት” በየቤቱ ቢከፈትና 24ሰዓት እየተንጫጩ አካባቢውን ቢረብሹና እድሜያቸውን ቢጨርሱ ጉዳዩ አይለም፡፡ ለዚህም ነው ዛሬ በዘመናችን ከጫት፣ ከሲጃራ፣ሺሻና ሉሎች አደንዛዥ ዕፆች ባልተናነሰ መልኩ ፈር ያጡ “አምልኮ ተቋማት”ና “መዝናኛዎች” ዜጎችን(በተለይም ወጣቱን) ማደንዘዣ እየሆነ የሚገኘው፡፡
አንዳንድ ጓደኞቼ ይህንን ሁለቱን( አምልኮ ተቋማትንና መዝናኛ ዘርፉን) የሀገራችን ዜጎች በሀገራችን ባለው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ተስፋ ቆርጠው የተቀላቀሉት ዘርፎች እንደሆኑና ወደውና ተረተው የተቀላቀሉት እንዳይደለ ይከራከሩኛል፡፡ ለምን እንደዚህ እንዳሉ ብጠይቃቸው ምላሻቸው የሚከተለው ነው፡፡ 
“አንደ ኢትዮጵያ ያሉት አምባገነን ፖለቲካ ስርዓት በሰፈነባት ሀገር ውስጥ ፖለቲካን መነካካት ከእሳት ከመጫወት አልፎ እሳትራት የሚያደርግ ስለሆነ ነው፡፡ ስለዚህ ዝም ብሎ መገዛት፣ በአምልኮ ስም መደበቅ ይሻላል፡፡” ጓደኞቼ ለጥቀውም “…ልክ እንደ እምነት ነጻነት ሁሉ ዜጎች( ይቅርታ ዜጋ መባል አልጀመረንም ለካ ተገዥዎች) በገዥው ስርዓት በኢኮኖሚው በፖለቲካውና በማኅበራዊ ዘርፍ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በተመለከተ የታዘቡትን ነገር በነጻነት መተቸት፣ አማራጭ ሀሳብ ይዘው መቅረብና ተከታይም ማፍራት ለሕይወት አስጊ በመሆኑ ያለው አማራጭ ኢግዚአብሔር ያውቃል ብሎ ዝም ማለትን አብዘኛው ሰው፤ በተለይም ወጣቱ ኃይል ስለተቀበለ ነው፡፡” ይላሉ ጓደኞቼ
እነም አልኳቸው ልክ የሚመስል አንጂ ልክ ያልሆነ ወሳኔ፡፡ 
ከላይ ጓደኞች የያዙት አቋም(አቋም ይዞ መሟገታቸውን ግን ወድጃለሁ፤ የማይሟገት ትውልድ አልጫ ነውና፡፡ መግት ሁሉ ግን ልክ አይደለም፡፡) ምንም እንኳን አምባገነናዊ ስርዓት መግቢያ መውጫ ያሳጣበት ሀገር ውስጥ ለሚኖሩ ጭቁኖች አማራጭ የሌለ ቢመስልም ቅሉ ዝምታ እራሱ ከጥፋት አያድንም፣ ዜጎችን የፈሩት መውረሱም ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ምክንያቱም አብዘኛው ጭቁን ህዝቦች ፈርተው ዝምታ ቢመርጡ ለውጥ ተፈጥሯዊ በመሆኑ ህዝብን ተባብረው ሲጨቁኑና ሲመዘብሩ የቆዩ አባገነኖች ቢያንስ እርስ በራሳቸው ደቧድነው(ህዝብ ባይነሳባቸውም) መፋጀት ሰለማይቀርላቸው ዝም ያለውም ጭቁን ህዝብ የገፈቱ ቀማሽ ከመሆን አይድንም፡፡ ሁለቱ የጠገቡ በሬዎች በሚፋጁበት ቦታ ያለው ሳር(ሰው፣ ቤት፣ ቤተ-እምነት፣ ባህላዊ ስርዓትና ቅርስ ወዘተ) እንዳልነበር ከመሆን አይድንም፡፡ ስለዚህ አስፈሪው ተናግረህም(ታግለህም) ሆነ ዝምታ መርጠህም ቢያንስ ይጎዳል፤ ሲሆንለት ደግሞ ከምድረ-ገጽ አጥፍቶ በነበር ያስቀራል፡፡ በመሆኑም በዚህም ሆነ በዚያ መጥፋት(ቢያንስ መጎዳት) የማይቀር ከሆነ ዝምታ መርጠን እንዲሁ በማያዛልቅ ዋሻ ውስጥ ገብቶ ከመቆየት ወጥቶ እየተናገሩ(እየታገሉ) ማለቅ(መጎዳት) የተሻለ ነው የሚል እምነት አለው የዚህ መጣጥፍ አዘጋጅ፡፡
የ“አምልኮ ተቋማት” በየስርቻው(በተለይ በሀዋሳ ከተማ ውስጥ) የመበራከቱ ምስጥር መንድር ነው?