Gudumaale

   Sidaamu Daga Budu Battala
Connecting Sidama People

የሲዳማ ህዝብ የዘመናት ትግል አጭር ታሪክና ወቅታዊ ሁኔታ

By DLL (From Facebook page of Selamu Bukana)


የሲዳማ ህዝብ ከ130 ዓመታት በላይ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ለማሰከበር ሁለ-ግብ መስዋዕትነት ከፍሎአል፡፡ በመክፈል ላይም ይገኛል፡፡

ዛሬም የህ.ወ.ሃ.ት ተወላጅ የሆነዉ ደ.ኢ.ህ.ዴ.ንም ዴሞክራሲያዊና ህገ-መንግስታዊ መብቶቹን በመርገጥ በሸፍጥና ጭካኔ በተመላበት አካሄድ እየገዛዉቆይቶአል፡፡

ደኢህዴን/ኢህአዴግ በሲዳማ ሕዝብ ላይ ከፈጸማቸዉ በደሎች በጥቂቱ:-

1. በህዳር ወር 1984 ዓ.ም የሲአን መሪዎች በሀዋሳ ከተማ ከስብሰባ አደራሽ ሲወጡ የተደራጀ ገዳይ ኃይል በማዘጋጀት በመኪናቸው ላይ ተኩስ ተከፍቶ በርካታ ንጹሀን የሲዳማ ልጆች ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡ የሲአን መሪ የሆኑት አቶ ወልደአማኑኤ ዱባሌ ለጥቂት ሲተርፉ ከእርሳቸዉ ጋር የነበሩ የአገር ሽማግሌና ዋቆ ኦሪሳ በከፍተኛ ደረጃ ቆስለው በህክምና ርብርብ ህይወታቸው ሲተርፉ ብዙዎቹ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡
2. በ1985 ዓ/ም ህዝብን ለማሸማቀቅ ታስቦ ወደ ሆሮሬሳና ያአኗ ጭሬ ወረዳዎች የተሰማራዉ
የደህዴን/ኢህአዴግ ገዳይ ኃይል በግፍ ከረሸናቸዉ የሲዳማ ታጋዮች መካካል ለአብነት ብቻ ጥቆቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል :-

☝ታጋይ ሱንባሶ ሱሩራ
☝ታጋይ ካንባታ የጤ
☝ታጋይ ወላ ጎሶማ
☝ታጋይ ሀጤሶ ጋማዳ
☝ታጋይ ሄላ ባናታ 
☝ታጋይ ማንሳ ሌዳሞ
☝ታጋይ በቀለ ላጊዴ
☝ታጋይ መለሰ መንደፍሮ
☝ታጋይ ማቴ ማሻሻ
☝ታጋይ ጫሌ አባቱን ለጊዜው ያልተገለጸ::

እቤታቸው በሰላም በተኙበት በሌሊት መንደሩን በማሸበር ተገድሎ አስክሪናቸዉ በአኗዋ ጭሪ ወረዳ እና በኦሮሚያ ክልል ድንበር ላይ በሚገኝ ሀምሌ ወንዝ ውስጥ ተጥለዋል።

3. በ1986 ዓ.ም በዚሁ ወረዳ ከቤታቸው ታፊነው ተወስደው በሀርቤጎና ወረዳ ሀፉርሳ በሚባል ጫካ ውስጥ እጃቸውን እንደታሰሩ በግፍ ተገድለውና በጅምላ ተቀብረዉ ከተገኙት መካከል ጥቂቶቹ:-

☝ታጋይ ደምሴ ጋዊዋ
☝ታጋይ ቱሚቻ ጋዊዋ
☝ታጋይ ዶያሞ ዲካ
☝ታጋይ ዲካ ጋንቡራና
☝ታጋይ ሹጉራ ናማሮ ሲሆኑ በወቅቱ የግዲያው ዋናው ተዋናይና ስልት ቀያሾች የስርዓቱ አገልጋይ የሲዳማ አመራሮችም ጭምር እንደነበሩ የአደባባይ ሚስጢር ነዉ፡፡

4. ሌላዉ በሲዳማሰላማዊ ህዝብ ላይ የተፈጸ ዘግናኝ የጅምላ ግድያ 
☝በግንቦት 16/1994 ዓ.ም (24,2002 Sidama Loqe Massacre) በመባል በዓለም ደረጃ የተመዘገበና ሰላማዊና ንጹሀን የሲዳማ ልጆች በመንግስት ወታደሮች የተፈጁበት፤
👉ከ50 በላይ በአንድ ጀንበር የተጨፈጨፉበትና 26 የቆሰሉበት
👉በሺዎች የሚቆጠሩ በጅምላ የታሰሩበት 
👉ዝርዝር ሁኔታውን የኢሰመጉ 51ኛ መግለጫዎች ቅጽ 2 ገጽ 284-291 መመልከት ይቻላል፡፡ እነዚያ የአስተዳደርና የፖለቲካ ስልጣን በመያዝያ ሲያስጨፈጭፉን የነበሩ የፖለቲካ ደላሎች ዛሬም አንደ እስስት መልካቸዉን በመቀያየር ለጠላት መሳሪያ ሆነዉ በመንቀሳቀስ በሲዳማ ላይ ዳግም የሞት ድግስ በማዘጋጀት ላይ ይገኛሉ፡፡

5. የሲዳማ ህዝብ ታሪካዊ ጠላት የሆነዉ የደቡብ ክልል መዋቅር ምንነት፤ ህገ-መንግስትንና የፈዴራል አወቃቀርን መርህ የጣሰ ነዉ፡፡

የኢትዮጵያ ህገ- መንግስቱ ምን ይላል?
====+++++======
☝በአንድ ላይሊዋቀሩ ይችላሉ ተብሎ የሚታሰቡ ብሄሮች፤ብሄረሰቦች ፍላጎት መሰረት ያደርጋል
☝የህዝቦች ስነ-ልቦናናመስተጋብር የባህልና የቋንቋ መቀራረብ ከግንዛቤ ዉስጥ ይገባል
☝የህዝቦች ጂኦግራፍካል አሰፋፈርና ለአስተዳደር ያለዉ ምቹነት ተፈላጊ መስፍርቶች ናቸዉ፡፡

ከዚህ አንጻር የደቡብ ክልል አወቃቀር ከህጋዊ መሰረትና አግባብ ዉጪ የተፈጸመ ነዉ፡፡

6. የደቡብ ክልል እንዴት ተመሰረተ:-
☝የቀድሞ 'ሲዳሞ' አስተዳደር፤
☝የቀድሞ ጋሞ ጎፋ አስተዳደር
☝የቀድሞ ከፋ አስተዳደር&
☝ከማአከላዊ ሸዋ አስተዳደር ሀይቆችና ቡታጅራን ጨምሮ አንድ ላይ በማድረግ በፖለቲካ ደላሎች ዉሳኔ ብቻ የተፈጠረ ጭፍልn ክልል ነዉ፡፡

👉ለፖለቲካ ቁማርና ስሌት ታሳቢተደርጎ ህዝብ ሳይመክርበት የተመሰረተ ክልል፡፡
👉ለሰፊው ህዝብ አሰተዳደራዊ ምቹነት ታስቦ ሳይሆን የደኢህዴን ቅጥር ካድሬዎች መፈንጫ ነጻ ኢምፓየር ወይም ምሽግ ለማዘጋጀት ታቅዶ የተዋቀረ አርትፊሻል ከልልነዉ፡፡
👉የሲዳማ ህዝብ በዚህ ሁኔታ ለ27 ዓመታት እንዲሸከመዉ የተፈረደበት ፖለቲካዊና መዋቅራዊ ቀንበር ነዉ፡፡

7. የደቡብ ክልል ለምን ተመሰረተ ዋናዓለማዉ ምንድነዉ?

☝የቀድሞ አራት የአስተዳደር ክልሎቸ: በወያኔ ኢህአዴግ አገዛዝዘመን ደግሞአምስት ክልሎች ማለትም ክልል 7፣8፤9፤10 እና 11 የነበሩ ባንድ ጀንበር ተጨፍለቀው ለምን አንድ ክልል ተደረጉ?

በግልጽ የሚታዩና ድብቅ ዓለማዋች አሉት፡፡

✋በቅጽበታዊ ዓለማ፡-

😁በአቶ ወልደ አማኑኤል የሚመራ ሲአን፤ በዳኛ ሙሉ መጃ የሚመራ የወላይታ ዴሞክራሲዊ ድርጅት፤ በፕሮ/በየነ ጴጥሮስ የሚመራ የሀዲያ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፤ በአሰፋ ጫሞ የሚመራ የጋሞ ጎፋ ዴሞክራሲዊ ድርጅት የሆነዉንና ደቡብ ህብረት በመባል የሚታወቀዉን የጋራ ግምባር ለማደከም፤

😁የደቡብ ብሄር ብሄረሶበችና ህዘቦች የአንድነት መሰረት፤ልዩነታችን ውቤታችን እያሉ ውስጥ ውስጡን ህዝብን እርስ እያባሉ የሚኖሩበት የከበርቴ ካድሬዎች ነጻ ግዛት ለመፍጠር

✋ ድብቅ ዓለማዎች፡-
☝የሲዳማ ራስን በራስ የማሰተዳደር ጥያቄ ዘመናትን የተሻገረ በመሆኑ በአንድነት ሽፋን የሲዳማ እራሱን ከሞግዝት አስተዳደር ነጻ ለመዉጣት የሚያደርገዉን ትግልና እንቅስቃሴ ለመቆጣጠርና በሁሉም ረገድ ማዳከምነዉ፡፡
ለዚህም መሴሪ ዓላማ የተጠቀሙበት ስልት
☝በሰበብ አስባብ የሲዳማ ነጻነት ታጋዮችን በግፍ መግደል፤ማሰር፤ ጥበበኞችንና አዋቂዎችን አገር ጥለው እንዲሰደዱ ማድረግ፤

☝በሲዳማ ህዝብ ስም የተቋቋሙ የልማት ማህበራትና ተቋማት ባሉበት እንዲቆሙ ወይም ጉልህ ህዝባዊ ልማት ማካሄድ ትተዉ የካድሬ መጦሪያ ሆነው እንዲያገለግሉ ወይም እንዲከስሙ ማድረግ፡፡

☝የሲዳማ ህዝብ ሰላማዊና ማንንም የማይገፋ፤ከሁሉም ብሄር ብሄረሰብ ጋር በፍቅር የኖረና እየኖረም ያለመሆኑን ልቦናቸው እያወቀ የካድሬን መንጋ በማሰማራት ለሲዳማ ህዘብ የማይመጥን የጠባብነት ታፔላ በመለጠፍ መሳደብ፤ ማሸማቀቅ የህዝብን ሞራል መንካት፡፡

☝ቋንቋና ባህላዊ እሴቶች እንዳያድጉ በአስተዳደራዊ መሰናክሎች መንገድ መዝጋት

✋2ኛ ድብቅ ዓለማና ዕቅድ

☝የአከባቢን ህዝብ በተለያዩ ሰበቦች መሬቱን እየቀሙ ከሀዋሳ ከተማ አከባቢ መግፋት

☝ቀስ በቀስ ቁጥሩን በመቀነስ፤በምትኩም የእኛ ወገን የሚሉትን በመተካት ማጆሪቲይ ማድረግ

☝የሲዳማን ተፈጥሮአዊ ባለቤትነትን በማሳጣት የፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ማንሳት በማይችል ደረጃ ማይኖሪቲይ እንዲሆን ማድረግ ነዉ፡፡
ለአብነት፡-
👉በተለያዩ ሰብዓዊ ፕሮጄክቶች ስም በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች እንዲ ፈናቀሉና ከሀዋሳ እንዲርቁ ተደርገዋል፡፡
👉የከተማ አስተዳደርን ስልጣን በክልላዊ ማእከላዊነት በመቆጣጠር አብዛኛው የመንግስትና የቀበሌ ቤቶችን ወገናችን ለሚሉአቸው አስተላልፈዋል፡፡በዚህ ሁኔታ ከሲዳማ ብሔር የሆነ ህብረተሰብ ለመፍጠር በጽናት ተንቀሳቅሰው አሳክተዋል፡፡የዚህ እኩይ እቅድ ተግባራዊነት በጽናት የታገሉላቸዉና ያስፈጸሙላቸዉ የሲዳማ ስም ሽፋን የሸጡንና የለወጡን፤ዛሬም ሊያጠፉን እየተንቀሳቀሱ ያሉት እነማን እንደሆኑ ለይቶ ማወቅ የትግላቸን አንዱ አካል ተደርጎ መወሰድ ያለበት ጉዳይ ነዉ፡፡

✋3ኛ ድብቅ ዓለማ

ሕወኸት ኢትዮጵያን ለመቶ ዓመታት ያለ ተቀናቃኝ ለመግዛት፡ ያስባል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ የማንነትና እራስን የማስተዳደር ጥያቄ ደግሞ ሁልጊዜም ቢሆን እንቅልፍ የሚነሳው ጉዳይ ነበር፡፡

በመሆኑም ኦሮሞን ለመቆጣጠር እንዲቻለው ደግሞ ሳይጠሩት አቤት ሳይልኩት ወዴት የሚሉ ከህዝብ የተጣሉ ወይም ህዝብ የማያውቃቸዉ ካድሬዎች የሚያስተዳደሩት ከልል መፍጠር ያስፈልገዋል፡፡
ለዚህ ደግሞ የደቡብ ሆድ አደርና ተላላኪ የፖለቲካ ደላሎች ምቹ ሆነው ተገኙለት።

ስለዚህ የሀዋሳን ከተማ ከሲዳማ ብሄር በማጽዳት አከባቢውን ጨምሮ ለፈዴራል ተጠሪ በማድረግ ምሽጉን በሀዋሳ በማድረግ የደቡብን ህዝብ በኦሮሞ ህዝብ ላይ አያዘመተ የመኖር ቅዠት ተግባራዊለማድረግነዉ፡፡

ይህም መሴሪ እቅድ ለማሳካት በሁሉም አቅጣጫ የሲዳማን የህልዉና ትግል ማክሰምና ከኦሮሞ ጋር የመደራደርና የመቀራረብ ወኔና ጉልበት እንዳይኖር ማድረግነዉ፡፡

በዋናነት የሲዳማ ህዝብ በጉርብትና፤ በስነ-ልቦና በባህል በኢኮኖሚ ትስስር በተለይም በዘር ግንዱ ምክንያት ድንገት የደቡብን ቀን በርሰብሮበመዉጣትከኦሮሞህዝብጋርግንባር ከፈጠረ የደቡብ ክልል ይፈርስና ለወያኔ አማራጭ ነጻ ምድር የማጣት ስጋት ለመቀነስ ነዉ፡፡

8. በደቡብ መዋቅር ምክያንት የሲዳማ ህዝብ ምን ተጎዳ? ☝ዴሞክራሲያዊና ህገ-መንግስታዊ የመብት ጥሰቶች ደረሱበት

ህግ ምን ይላል? 
አንቀጽ 39 ንአሁስ አንቀጽ 1
👉ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሄር፤ብሄረ-ሰብ ወይም ህዝብ የራሱን እድል በራሱ የመወሰን መብቱ በማንኛዉም መልኩ ያለገደብ የተጠበቀ ነዉ ይላል፡፡

👉ከዚህ ተቃራኒ በሆነ መልኩ የሲዳማ ህዝብ ያለ ሞግዝት እራሱን በራሱ ለማስተዳደር የሚያስችለዉን ክልል የመሆን ህጋዊ ጥያቄ በ1997 ዓ/ም አቀርቦ ካድሬዎችን በማባበልና ስልጣን በማደል የደቡብ ካድሬ ሁሉ ተረባረበበት
👉ዛሬም የሲዳማህዝብ ለሁለተኛ ጊዜ በ2010 ያቀረበዉ ክልል የመሆን ጥያቄ በተለያየ ስልት እየዘገየ ይገኛል፡፡

👉የሲዳማ ጥያቄ ዘመን ተሸጋሪ ሆኖ ሳለ ሌሎች ዞኖችና ወረዳዎች ሁሉ በዘመቻ እንዲጠይቁ እየተቀነባበረ የከልል ጥያቄ ተራ ፋሽን እሰከሚመስል ያደረጉ የደቡብ ክልል የሴራ ፖለቲከኛ ካድሬዎች እጅ እንደሆነ ለሁሉም ግልጽ ነዉ፡፡

☝የሲዳማ ህዝብ ክልል ከተሰጣቸዉ ጋር በህዝብ ሲነጻጸርምን መልክ አለዉ?

የ2015 (እ.አ.አ ቆጣጠር) በወጣዉ የመንግስት መረጃ መሰረት
👉ኦሮሞ 35.4 ሚሊዮን
👉አማራ 21.1 ሚሊዮን
👉ሱማሌ 5.6 ሚሊዮን
👉ትግራይ 5.2 ሚሊዮን
👉ሲዳማ 4.5 ሚሊዮን
👉አፋር 1.7 ሚሊዮን
👉በንሻንጉል ጉምዝ 1 ሚሊዮን
👉ጋምበላ 409000 
👉ሀሬሪ 232000 ሆነዉ ሁሉም የራሳቸዉ ክልል አላቸዉ፡፡

ለምንድን ነዉ የሲዳማ ህዝብ የተከለከለው ምክንቱ ከላይ የተገለጹት የሸፍጥ ፖለቲካ ነዉ፡፡ ከዚህ አንጻር ገና ከጅምሩ ደቡብ የሲዳማን ህልዉና ለማክሰም ታሰቦ የተዘጋዘጀ ካንሰር ማለት ነዉ ይቻላል፡፡

9.የሲዳማ ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ለምን የህሊዉና ጉዳይ ሆነ?

☝ፖለቲካዊና ሰብአዊ ምክንቶች 
👉የሲዳማ ህዝብ ቁጥር 4.5 ሚሊዮን ሆኖ ሳለ በደቡብ ከልል መንግሰት ዉስጥ በፖለቲካዉም ሆነ በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ የመወሰን ስልጣን(20% ብቻ) ስለሆነም በሁሉም ረገድ የህዝባችንጉዳይ ወሳኝ ትኩረት አጥቶአል፡፡

👉በቂ የፖለቲካ ስልጣንና ውክልና ስሌለዉ የሲዳማ ህዝብ በአደባባይ ተጨፍጭፎአል፤ታስሮአል፤ ተሰዶአል
👉ልማት ጨርሶ ቆሞአል፤ በገጠርም ሆነ በገጠር ድህነት ከ80% በላይ ደርሶአል፤ የምግብ ዋስትና አዳጋ ላይ ወድቆአል ።
👉ሲዳማን ለመደለል የሚሰጡ የክልል ርእሰ መሰተዳደርና የከተማ ካንቲባሹመቶች ተጽእኖ የመፍጠር አቅም የሌላቸው የይስሙላ ወንበሮች ስለሆኑ ለህዝብ ልማት ጉዳይ ያልፈየዱ ናቸዉ፡፡

☝ማህበራዊና የፍትሀዊነት ምክንያቶች 
አሁን ካለዉ የሲዳማ ህዝብ ቁጥር 70 ከመቶ የሚሆነዉ ከ14 እስከ 34 ዓመት እድሜ 2.5 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች ናቸዉ፡፡

ከእነዚህ 80% በላይ ስራ የላቸዉም
👉ይህንን ኃይል ከሞግዝት አስተዳደር ተጽእኖ ዉጪ በልዩ ሁኔታ በእዉቀትና በጥበብ ማስተዳደርና መምራት ካልተቻለ በቀጠናዉ ማህበራዊ ቀዉስ የመፍጠር አቅሙ እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ ለመገመት ነቢይ መሆንን አይጠይቅም፡፡

👉በየዓመቱ ከዩኒቬርሲቲ የሚመረቁና በሲዳማ የሚፈጠረ ያለዉ የስራ እድል የሰማይና የምድርን ያህል ይራራቃል፤
የገጠር መሬት ተከፋፍሎ ከማለቁም በላይ ምርታመነቱ በእጅጉ በመዉደቁ አርሶ አደሩን እራሱን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ የማይችልበት ደረጃ ደርሶአል፡፡

👉የአርሶ አደር ልጆች ከገጠር እየፈለሱ የከተማ ጎዳናዎችን አጨናንቀዋል፤ልመናና ሌብነት ተንሰራፍቶአል፤
ሲዳማ ለፌዴራል መንግስት ያለዉ የኢኮኖሚ አሰተዋጽኦ ከፍተኛ ቢሆንም የደቡብ መንግስት የሚሰጠዉ ባጄት ከመደበኛ ደምወዝ የሚዘል ባለመሆኑ የልማት ስራዎች ቆመዋል፤
👉ስራ ፈጣሪዎች፤ ለወቅታዊ ችግር ወቅታዊ ምላሽ የሚሰጡ አዋቂዎችና ጥበበኞች ተሰደዉብናል፤ ወይም በቁም ታሰረውብናል፤ ፖለቲካዉን የሚዘዉሩት አብዘኛዉ የካድሬ መንጋ አምራችና ስራ ፈጣሪዎች ሳይሆኑ ጥገኛ በላተኞች ሆነዋል፡፡

☝ከልል የመሆን ጉዳይ የህልዉና ጥያቄ ነዉ፡፡ ለምን?
የደቡብ የካድሬ መንግስት ለሲዳማ ህዝብ ጥላቻንና ወድቀትን በመሰበክ ሆን ብሎ ህገ መንግስታዊ የመብት ጥሰቶችን ፈጽሞበታል።

☝የሌቦችና የዘራፊዎች ዋሻ በመሆን ከላይ እሰከ ታች በተደረጀ ተቋማዊ ዝርፊያና ሌብነት በመፈጸም አቆርቁዞታል፤ ሲዳማን የሰረቁ፤ የገደሉ መደበቂያ ዋሻ ነዉ፡፡ደቡብ የዘራፊዎችና የገዳዮች መማጸኛ ማእከል ነዉ፡፡
መንግስታዊ አገልግሎት አሰጣጡ ደካማና ዘገምተኛ በመሆኑ ህዝብን አሰመርሮታል፤

☝የአመራርና የሙያ ብቃት ያላቸዉን ባለስልጣናትን የሚፈጠር ሳይሆንለግል ጥቅምናክብር ህሊናቸዉንየሚያሸጡአደር ባይ መሪ ተብዬዎች የሚፈለፈበት ዋሻ ሆኖአል።

☝ስልጣን በሙያ ብቃትና ችሎታ ሳይሆን በእጅ መንሻ በጉቦ የሚታደልበት የሙሴኞቻ መዋቅር ነዉ፡፡

በተለያየ መንገድ የደኢህዴን ካድሬ የሲዳማን የጥቃት ዓለማ በማድረግ ተሳድቦ ለተሳዳቢዎች አሳልፎ ሰጥቶታል
በ2004 ዓ/ም ሜትሮፖሊታያን ከተማችንን እንዴት እንምራዉ በሚለዉ የካድሬ ሰነድ ላይ የሲዳማ ህዝብ ትግል እንደ አገዳ እሳት ብልጭ ብሎ ወዲያዉ ስለሚጠፋ አሳሳቢ አይደላም በማለት በአደባባይ ተሳድበዋል፡፡

የሲዳማን ህዝብ የግል ንብረት አድርጎ ዳግም በባርነት አፍኖ ለመግዛት የሚያስችል በምንም መልኩ ሞራላዊና ፖለቲካዊ ቁመና የለዉምና ያለፍላጎት የተፈጸመ ጋብቻ ያለፍላጎት በፊቺ መደምደም ያለበት መዋቅር ነው፤

10. የሚጠበቀዉ ሪፈሬንደም ለምን ይዘገያል? ባንዳንድ መድረክ እንደሚነገረዉ የጥናት ዉሳኔ በመጠበቅ
ህጋዊ አካሄድ ያጠናቀቀ ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ በአዲሰ አጥኝ ቡድን እንደ አዲስ ጥያቄሊታይ አይችልም፤ አይገባምም፤
☝ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩ አይነቀንቁካልሆነ በስተቀር፤ የሲዳማ ጥያቄ የሚመለሰዉ በስራ ላይ ባለዉ ህገ-መንግስት መሰረትና ሂደቱን ባጠናቀቀበት ደራጃ ብቻ ነዉ፡፡
ደግሞም ለዚህ ጉዳይ ተብሎ የነበረዉን ህግ ማሻሻል ማለት በራሱህገ-መንግሰትን መጣስ ይሆናል፡፡ ህግደግሞ ወደ ኋላ ተመልሶ አይሰራምና፤
☝የሲዳማ ጥያቄም መጠናቀቅ ያለበት አሁን ከደረሰበት ደረጃ በክልል ምክር ቤት አደራጅነት በምርጫ ቦርድ የቅርብ ክትትል ብቻ ነዉ፡፡

አምስት ሚለዮን በላይ የሆነ የሲዳማ ህዝብ በራሱ ጉዳይ ባለዉ ህገ-መንግስት መሰረት ስለ ራሱ ጉዳይ እራሱ መወሰን አይችልም ማለት የግፍ ግፍና የበደል በደል ነዉ፤የትምክህትም የመጨረሻ ጫፍ መርገጥ ነው፡፡

11. የሪፌረንደም ጉዳይ/ኳሱ የት ጋ ነዉ ያለው;
የኢትዮጵያ ህግ ምን ይላል?
✋የፌደራል መንግስት ህገ-መንግስት አንቀጽ 47 ንኡስ አንቀጽ 3
የማንኛዉም ብሄር፤ብሄረ-ሰብና ህዘብ የራሱን ክልል መመስረት ስራ ላይ የሚዉለዉ 
ሀ. ክልል የመመስረት ጣያቂዉ ብሄር ፤በሄረ-ሰበ ወይም በህዝቡ ም/ቤት 2/3ኛ ድምጽ 
ተቀባይነት ማግኘት ሲረጋገጥ፤ ጥያቄዉ ለክልል ም/ቤት ሲቀርብ 
ለ. ጥያቄ የቀረበለት የክልል ም/ቤት ጥያቄዉ በደረሰዉ ባንድ አመት ጊዜ ዉስጥ ለጠየቀዉ ብሔር፤ብሄረ-ሰብ ወይም ህዝብ ህዘበ ዉሳኔ ሲያደራጅ
ሐ. ክልል የመመስረት ጥያቄዉ በብሄሩ፤ ብሄረ-ሰቡ ወይም ህዝብ፤ ህዘበ ዉሳኔ በአብላጫ ድምጽ ሲደገፍ
መ. የክልሉ ም/ቤት ስልጣኑን ለጠየቀዉ ብሄር፤ብሄረሰብ ወይም ህዝብ ሲያሰረክብ
ሠ. በህዝበ ዉሳኔ የሚፈጠረዉ አዲስ ክልል ጥያቄ ማቅረብ ሳያስፈልገዉ በቀጥታ የኢትዮጵያ ፈዴራላዊ ዴሞክራሰሲዊ ረፑብሊክ አባል ሲሆን ይላል፡፡

ከዚህ ህግ አንጻር ሪፌረንደም ማደራጀት(ባጄት፤የሰዉ ኃይል፤ሎጂስትክ) ያለበት የክልል ም/ቤት ነዉ፡፡ ታዲያ የሲዳማ አመራሮች ምርጫ ቦርድ ደጅ የሚጠኑት ለምንድን ነዉ?የገዳዩ ባለበት ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል እንላለን፡፡

የምርጫ ቦርድ ኃላፊነት የሪፈሬንደሙን አፈጻጸም መቆጣጠር፤መከታተልና ዉጤቱን ይፋ ማድረግ ብቻ ነዉ

12. ካሁን በኋላ ምን እንጠብቅ ምን ሊሆን ይችላል?
መላምት አንድ
☝እንደሚሰማዉ ሁሉ ዘመን ያሰቆጠረ የሲዳማ ጥያቄ በጥናት ይመለስ ይባል ይሆናል!!
ለዚህ የሚኖረን ምላሽ ምን ይሆናል;
👉ከወዲሁ ክልላዊ መዋቅር ጥናት ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቅ፡፤
👉ዓመታዊ ባጄት ታሳቢ ከወዲሁ ማዘጋጀት ህጋዊ አሰራሮችን ለማጠናከር የሚያስቸል ስልጠና ማካሄድ፤
የፖሊስና የጸጥታ ኃይል በድንበርና በከተሞች ማጠናከር፤ 
የጊዜ ገደቡ በላቀ ማግስት ጀምሮ የሲዳማ መንግስት መዋቅር ከደቡብ መንግሰት ሙሉ በሙሉ በማቋረጥ የራሱን ክልል ማወጅ፡፡
#መላምት 2
☝ምርጫ ቦርድ በፕሮገራሙ መሰረት ሪፈሬንደም ሊያካሂድ ይችላል; ይህ የሚሆን ከሆነ ምርጫ ቦርዱ የአፈጻጸም መርሀ-ግብር ከወደዲሁ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ 
☝በሲዳማ ህዝብ በኩል ሊወሰዱ የመገባ እርምጃዎች በየወረዳዎች ሆን ተብሎ የሚነሱ ዉዝግቦች ሙሉ በመሉ ማቆምና፤አስተማማኝ የጸጥታ ድባብ መፍጠር፤
ለምርጫዉ ሂደት የሚያግዝ ሎጂስቲክ ማመቻቸት
ስለ ሪፈሬንደሙ ለህዝቡ ግንዛቤ የማስጨበጫ ስራ ማካሄድ
✋ከክልል ጋር የሚያያዙ የአሰተዳደርና የፕሮቶኮል ስራዎችን በዘርፉ ባለሙዎች ከወዲሁ ማመቻቸት
እንደ መውጫ ሀሳብ

✋የደቡብ ክልል ም/ቤት በለመደዉ የተንኮልና ሴራ ፖለቲካ በመጠቀም የህዝቡን ትእግሰት መፈታተኑ ለማንኛችንም አይበጅምና ቆም ብሎ ቢያስብበት ይሻለዋል እንላለን፡፡
የሲዳማን ህዝብ ያመረቀዘ ቁስል በመነካካት ህዝቡን ወደልተፈለገ አቅጣጫ መግፋት ላለፉት 27 ዓመታትም ጥፋትን እንጂ ልማትን አላመጣም፡፡ በመሆኑም የፖለቲካ አሻጥሩ እንዲያቆም እናስጠነቅቃለን፡፡

✋ ትእግሰት የአሰተዋይነትና የአርቆ አሳቢነት ምልክት እንጂ ፍርሃት አይደለም፡፡ ምንም መስዋእት ቢጠይቅ ሶማሊያ ድረስ ለወራት በእግር ተጉዞ ተመልሶ ደርግን የተጋፈጠበትንና ከከፈለዉ ዋጋ አይበልጥም፡፡ ሶማሊያ ድረስ ሄዶ በወትድርና ሰልጥኖ ድርግን የተዋጋዉና በ10 ሺዎች ህይወትና ንብረት የገበረዉ፤በሀዋሳ ከተማ የተጨፈጨፈዉ የሲዳማ ህዝብ ከማንም ምንም ፈልጎ ሳይሆን መብቱ በህገ-መንግስቱ መሰረት እንዲከበርለት ብቻ ነዉ፡፡

✋ደግሞም ሰበብ እየፈለጉ የሲዳማ ህዝብ በጉርብትና፤በስነ-ልቦና፤ በባህል በኢኮኖሚ ትስስር በተለይም በዘር ግንድና በደም የተሳሰረን ከኦሮሞን ህዝብ ጋር የማጋጨት ተንኮልና የፖለቲካ ቁማር በፍጥነት ሊቆም ይገባል፡፡ ከኦሮሞ ወንድሞቻችን ጋር ይህን ተንኮል ለማክሸፍ በመናበብ መንቀሳቀስ ደግሞ ነገ ዛሬ ሊባል አይገባም እንላለን፡፡
ይልቁንም ገዥዎቻችን የሚዘጋጁልን የተንኮል ኬላ ሰባብረን የኦሮሞና የሲዳማ ህዝቦች አንድነት ተፈጥሮአዊ እንደሆነ ለጣላትም ለወዳጅም በተግባር ማሳየት ያለብን ዘመን ቢሆን አሁንና አሁን ብቻ ነዉ፡፡ በሲዳማና በኦሮሞ ህዘቦች መካከል የሚቀበሩ አርቲፊሻል የፖለቲካ ፈንጅዎችን ማምከን የሚችሉት ሁለቱ ወንድማማች ህዞቦች ከምን ጊዜም በላይ የነበራቸዉንና ያላቸዉን ባህላዊና ማህበራዊ ትስስር ማጠናከር ሲችሉ ብቻ እንደሆነም አስረጂ አያሰፈልገንም፡፡
ለዚህም እዉነተኛ የሀይማኖት መሪዎች፤እዉነተኛ ባህላዊ ሽማግሌዎች፤ አባገዳዎች፤ ምሁራን፤ አርሶ አደሮች በግልም ሆነ በቡድን ድርሻችንን ለመወጣት በተቀናጀ ሁኔታ መንቀሳቀስ አለብን፡፡

✋በመጨረሻም ደኢህዴን ማስተዋል ያለበት ጉዳይ ቢኖር የሴራ ፖለቲካ ለአሮጌዉ ኢህአዴግም ወድቀትና ሞት እንጂ ትንሳኤ እንዳልሆነለት ነዉ፡፡ስለሆነም የሲዳማ ህዝብም ሆነ ሌሎች ህዝቦች ከባለስልጣናት ተለክቶ በሚሰጥ ቁራሽ መብት ብቻ ይኖራሉ ብሎ ማሰብ የዋህነት ነዉ፡፡

✋ሁላችንም ወደ ፊት በሰላም አብረን መቀጠል ካለብን የህዝቦችን ፍትሃዊና ህገ-መንግስታዊ ጥያቄዎችን በህገ-መንግስት አግባብ ብቻና የህዝብንየልብ ቁስል በሚሽር መልኩ መሆን አለበት፡በመጨረሻም ሀሳቡን የምደመድመዉ

✋በሀገሪቱ ህገ-መንግስት ተማምነንና አንድ ቀን መፍትሄ ይገኛል በማለት ለሞት ለእስራት፤ለሰደት ተዳርገናል፤ ይህ ባይሆን ኖሮ ቁርጣችንን አዉቀንእግዚአብሄር እሰከሚታደገን ድረስ የሚፈራረቁብንን የኢትዮጵያን ፋርኦኖችን የባርነት ቀንበር ተሸክመን ለመኖር መወሰን ነበረብን ማለት ነዉ፡፡

👉ስለሆነም ሠፊዉ የሲዳማ ህዝብ ስጋት ዉስጥ መግባትን በመተዉና ጥቃቂን የጎንዮሽ ጉዳዮችን ጨርሶ በማዉገዝና እንድነቱን ከምን ጊዜም በላይ ባማጠንከር ደረጃ በደረጃ የተቀመጡ ሰላማዊና ስልታዊ የትግል ታክትኮችን ተግባራዊ ለማድረግ መዘጋጀት አለብን፡፡ ትግላችን ሊመክንና አደጋ ሊፈጠር የሚችለዉ አንድነትን የሚያናጉ አጨናጋፊ አካሄዶችን መቋቋምና ማሰወገድ ካልቻልን ብቻ መሆኑን አዉቀን ዘላለም እየሞትን ከምንኖር አንዴ ዋጋ ከፍለን ለዘላለም በነጻነት ለመኖር መወሰን ያለብን ጊዜ ቢኖር አሁንና አሁን ብቻ ነው ።

ሀዋሳ-ሲዳማ-ኢትዮጵያ
ጥር 19/2011 ዓ.ም